Burien የህዝብ ደህንነት ቀረጥ መረጃ

ማጠቃለያ

የBurien መራጮች፣ ህዳር 2025 በሚያደርጉት አጠቃላይ ምርጫ የBurien የህዝብ ደህንነትን በገንዘብ ለመደገፍ የመወሰን እድል ይኖራቸዋል።

ማህበረሰቡ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች ጋር በተሻለ ሁኔታ ለማጣጣም የ"ለህዝብ ደህንነት የቀረጥ ገደብ ማንሳት (Levy Lid Lift for Public Safety)" እርምጃ (የCity of Burien አስተያየት ቁጥር 1) የተዘጋጀው ከሁለት አመት በላይ የማህበረሰብ ተሳትፎ፣ እንዲሁም የBurien ከተማ ሰራተኞች ምርምር እና እቅድ ለBurien ከተማ ምክር ቤት ከቀረቡ በኋላ ነው።

በህብረተሰቡ የተለዩ ሦስቱ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች በምርጫው ላይ በትክክል የተንፀባረቁ ናቸው፦

  • የቤት እጦትን፣ የአእምሮ ጤና ቀውስን እና ህዝባዊ መድሃኒቶችን መጠቀም ለመቅረፍ የፖሊስ የጋራ ምላሽ ሞዴልን መጠበቅ እና ማስፋፋት
  • የጋራ ምላሽ ሰጪ ቡድኖችን ለመደገፍ፣ የአሁኑን የፖሊስ ሰራተኝት ደረጃ መጠበቅ እና ተጨማሪ የፖሊስ መኮንኖችን መቅጠር፣ በከተማው ውስጥ ያሉ ፓትሮሎችን ለመጨመር እና የማህበረሰብ ወንጀል መከላከል ፕሮግራሞችን ለመደገፍ ተጨማሪ የፖሊስ መኮንኖችን መቅጠር
  • መሠረተ ልማት እና ተጨማሪ የመንገድ መብራቶች በማሻሻል ደህንነቱ የተጠበቀ ጎዳናዎችን እና የእግረኛ መንገዶችን መፍጠር

 

በምርጫ ወረቀት ውስጥ ያለው

የእርምጃው ጽሑፍ እንዲህ ይነበባል፡-

 

ምክረ ሀሳብ ቁጥር 1 ለሕዝብ ደህንነት የቀረጥ ገደብ ማንሳት

ለፖሊስ ሰራተኞች፣ ለጋራ ምላሽ ፕሮግራሞች እንዲሁም ለጎዳናዎች እና ለእግረኛ መንገዶች ደህንነት ጨምሮ ለህዝብ ደህንነት የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ የBurien ከተማ ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 874 አጽድቋል። ይህ እርምጃ በ2026 የከተማውን መደበኛ የንብረት ግብር ከፍተኛውን ቀረጥ ከ$0.95/$1,000 ወደ ከፍተኛው መጠን $1.90/$1,000 ይጨምራል። ከ2027-2031 የከተማው አጠቃላይ መደበኛ የንብረት ግብር ቀረጥ እስከ 6% የሚሆነውን ገደብ አስቀምጧል። አረጋውያን፣ አርበኞች እና ሌሎች በተሻሻለው የዋሽንግተን ህግ (Revised Code of Washington, RCW) 84.36.381 ለተጠቀሱት ነጻ የሚደረጉ ይሆናል።

ይህ ሃሳብ ይጸድቃል፡- 

  • አዎ 
  • አይ

የማብራሪያ መግለጫ

ከፀደቀ፣ ይህ ሃሳብ ከ2026 ጀምሮ በRCW 84.55.010 ከተደነገገው ገደብ በላይ City of Burien ("ከተማዋ") ለህዝብ ደህንነት አገልግሎቶች እና ስራዎች መደበኛ የንብረት ግብር ቀረጥ እንዲጨምር ይፈቅዳል። ከዚህ የቀረጥ ገደብ መነሳት የሚሰበሰብ ማንኛውም ገንዘብ በከተማው በራሱ ልዩ የገቢ ፈንድ ውስጥ ይያዛል። በዓመት በአማካይ ከ5 እስከ 8 በመቶ የሚደርሱ የህዝብ ደህንነት ወጪዎችን ለመቅረፍ ከተማው ይህንን ቀረጥ ሀሳብ ያቀርባል፤ የንብረት ግብር ገቢ ግን በዓመት አንድ በመቶ ብቻ ይጨምራል። ያለ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ፣ ከተማው አሁን ያለውን የአገልግሎት ደረጃ ማስቀጠል ወይም እያደገ የመጣውን የህዝብ ደህንነት ፍላጎቶች ማሟላት አይችልም። 

ከቀረጥ የሚገኝ ገንዘብ የቤት እጦት፣ የአእምሮ ጤና ቀውስ እና የመድኃኒት አጠቃቀም ለመፍታት የፖሊስ የጋራ ምላሽ ሞዴልን ለመጠበቅ እና ለማፋፋት፤ የጋራ ምላሽ ሰጪ ቡድኖችን ለመደገፍ፣ በከተማው ውስጥ ያሉ ፓትሮሎችን ለመጨመር እና የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል የመከላከል ፕሮግራሞችን ለመደገፍ አሁን ያለውን የፖሊስ አባላት ደረጃ ጠብቆ ማቆየት እና ተጨማሪ የፖሊስ መኮንኖችን ለቅጠር፤ እንዲሁም በመሠረተ ልማት እና ተጨማሪ የመንገድ መብራቶች በማሻሻል ደህንነቱ የተጠበቀ ጎዳናዎችን እና የእግረኛ መንገዶችን ለመፍጠር ድጋፍ ያደርጋል። 

የመጀመርያው አማካኝ የቀረጥ ተመን ጭማሪ ከተገመተው የንብረት ዋጋ $0.79519/$1,000 ወይም፣ $596,000 የሚገመት ዋጋ ላለው ቤት፣ በግምት $39.50 በወር (ወይም በዓመት $473.90) ይገመታል። 62 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የሆናቸው ወይም የአካል ጉዳተኞች እና ዝቅተኛ ገቢ መስፈርቶችን የሚያሟሉ የቤት ባለቤቶች በRCW 84.36.381 ላይ እንደተገለጸው ከንብረት ግብር ነፃ መሆን ይችላሉ።

 

የጊዜ ሰሌዳ

ሰኔ 2025

  • የድምጽ መስጫ ቋንቋ ለማጽደቅ ወደ ከተማው ምክር ቤት ቀርቧል

    ላይ 2025

  • የከተማው ምክር ቤት የመጨረሻውን የድምፅ መስጫ ቋንቋ በስምምነት አጀንዳ ውስጥ ይመለከታል
  • ኮሚቴውን ለመደገፍ እና ለመቃወም ማመልከቻ Burien ነዋሪዎች ክፍት ይሆናል
  • የከተማው ምክር ቤት የሚደግፉ እና የሚቃወሙ የኮሚቴ አባላት ይሾማል

ገስት 2025

  • ከተማው የሚከተሉትን ወደ King County ምርጫዎች ያቀርባል
    • የቀረጥ ገደብ የማንሳት ውሳኔ
    • የሚደግፉ እና የሚቃወሙ የኮሚቴ ተሿሚዎች
    • የማብራሪያ መግለጫ
      • ኮሚቴዎች የሚደግፉ እና የሚቃወሙ መግለጫዎችን ወደ King County ያቀርባሉ
      • ኮሚቴዎች የማስተባበያ መግለጫዎችን ወደ King County ያቀርባሉ

    ክቶበር 2025

  • የከተማው የህዳር አጠቃላይ ምርጫ ማስታወቂያ የመጨረሻ ቀን

    ቨምበር 2025

  • የምርጫ ቀን ህዳር 4 2025 ነው

 

የሚደግፉ እና የሚቃወሙ ኮሚቴዎች

የBurien ነዋሪዎች የሚደግፍ ወይም የሚቃወም ኮሚቴ አባል ለመሆን እንዲያመለክቱ ተጋብዘዋል። የከተማው ምክር ቤት ለእያንዳንዱ ኮሚቴ እስከ ሶስት አባላት ሹመዋል። እያንዳንዱ አባል በሚከራከርበት ቦታ በግል ማመን አለበት።

የኮሚቴው አባላት በመራጮች በራሪ ወረቀት ላይ የሚታተም ለKing County በቀረበው ሀሳብ ላይ የኮሚቴዎቻቸውን አቋም የሚያንፀባርቅ መግለጫ (የተቃራኒ ኮሚቴውን መግለጫ የሚቃወሙ) የማውጣት ሃላፊነት ነበረባቸው።  

ኮሚቴውን ለመደገፍ እና ለመቃወም ማመልከቻዎች ማስገባት ሐምሌ 10 2025፣ ሰዓት 11:59 p.m. ይዘጋል።

 

የመራጮች መረጃ

ስለ መራጮች ምዝገባ፣ የምርጫ ቀነ-ገደቦች፣ ተደራሽነት እና እንዴት ድምጽ መስጠት እንደሚችሉ የበለጠ ለማወቅ፣ King County የምርጫዎሽ ድህረገፅ ይጎብኙ።

 

ኦክቶበር 13፣ 2025 ተሻሽለዋል