Immigration Resources amharic

የCity of Burien፣ በቡሪን፣ በWashington State፣ እና በዚች ሀገር ውስጥ ኑሮ ለሚያበለፅጉ ጎብኚዎቿን፣ ስደተኞችን፣ በመጠለያ ውስጥየሚኖሩ ስደተኞ እንዲሁም ነዋሪዎቿ  ይደግፋል።

Washington State ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጽህፈት ቤት (Washington State Attorney General’s Office) የክልል እና የአካባቢ ኤጀንሲዎች ምን እንዲያደርጉ እንደሚፈቀድላቸው ማብራሪያ የሚሰጠውን የWashington የስራ ደንብ መጠበቅ (Keep Washington Working Act) በተመለከተ መመሪያ ይሰጣል።

በ 2017፣ Burien City Council ማንኛውም የCity of Burien ሰራተኛ ወይም ሃላፊ የግለሰብን የኢሚግሬሽን ሁኔታ እንዳይጠይቅ የሚከለክለውን ድንጋጌ ቁጥር (Ordinance No.) 651 አጽድቋል።

በ2026፣ የከተማው ምክር ቤት ስደተኞች እና ስደተኛ ነዋሪዎች፣ ጎብኝዎች እና ሰራተኞች የሚደግፍ እና ለBurien community ያበረከቱትን አስተዋፅዖ የሚቀበል ውሳኔ ቁጥር (Resolution No.) 531 አጽድቋል።

ሁሉም ሰው የኢሚግሬሽን ሁኔታ፣ ዘር ወይም የፆታ ማንነት ምንም ይሁን ምን፣ የመንግስት አገልግሎቶችን ማግኘቱን እንዲቀጥል፣ የCity of Burien ሰራተኞች ማንኛውንም የፖሊሲ ለውጦች ካሉ ከአዲሱ አስተዳደር ጋር በቅርበት እየተከታተሉ ይገኛሉ፣ እንዲሁም ትክክለኛ መረጃ ለመስጠት በንቃት እየሰሩ ነው።

City of Burien፣ መብቶችዎን እንዲያውቁ እና በክልልም ሆነ በአካባቢ ደረጃ ለስደተኛ ማህበረሰብ የተሰጡትን ጥበቃዎች እንዲጠቀሙ ያበረታታዎታል።

የኢሚግሬሽን እና የጉምሩክ ማስፈጸሚያ እንቅስቃሴን በተመለከተ የማህበረሰብ ስጋቶች

የCity of Burien፣ የኢሚግሬሽን እና የጉምሩክ ማስፈጸሚያ (U.S. Immigration and Customs Enforcement, ICE) እንቅስቃሴን በተመለከተ የማህበረሰቡን ስጋቶች ያውቃል። ይህ ክፍል፣ City of Burien ምን መቆጣጠር እንደሚችል እና እንደማይችል እንዲሁም በአሁኑ ጊዜ ምን እየሰራ እንደሆነ አጠቃላይ መረጃ ይዟል።

City of Burien የማይቆጣጠረው ነገር፦

  • በፌዴራል ሥልጣን ስር የሚሰሩ የፌዴራል ኤጀንሲዎች። የቡሪን ከተማ፣ የፌዴራል ስራዎችን መመሪያ አይሰጥም እና የፌዴራል እንቅስቃሴን አስቀድሞ ማስታወቂያ አይደርሰውም። 
  • ከBurien Police Department ሃላፊዎች እና King County Sheriff’s Office ተወካይ በተጨማሪ፣ የCity of Burien ሰራተኞች በICE እንቅስቃሴ ውስጥ ጣልቃ መግባት አይችሉም።

የCity of Burien የሚቆጣጠረው፦

  • አሁን ባለው ሁኔታ ውስጥ፣ ቡሪን ለማንኛውም የኢሚግሬሽን ማስፈጸሚያ የሚውል የFlock ካሜራዎችን ጨምሮ የቪዲዮ ክትትልን አይጠቀምም ወይም አያበረታታም።
  • በKing County Sheriff’s Office፣ የBurien Police Department እና የCity of Burien ሰራተኞች የፌደራል የሲቪል ኢሚግሬሽን ህግን አያስፈጽሙም።
  • በWashington የWashington ስራ ደንብ ማስቀጠል (Keep Washington Working Act) በሲቪል ኢሚግሬሽን ማስፈጸሚያ ላይ የክልል እና የአካባቢ ህግ አስከባሪዎችን ተሳትፎ ይገድባል፤ እንዲሁም ስለ ትብብር እና መረጃን ስለመጋራት ግልጽ ደንቦችን ያወጣል።
  • የCity of Burien ሲስተሞቿ እና መረጃዎቿን ትጠብቃለች። በCity of Burien የተያዘ ማንኛውም መረጃ መጠየቅ፣ ለህዝብ ይፋ ማድረጊያ የተሻሻለው የWashington ደንብ (Revised Code of Washington, RWC) ምዕራፍ 42.56 የመጠየቅ ሂደት መከተል አለበት። 

የCity of Burien ምን እያደረገ ነው፦

  • የCity of Burien የኢሚግሬሽን ወይም የነዋሪነት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን በቡሪን ውስጥ የሁሉም ሰው መብት መከበራቸውን ለማረጋገጥ ህጋዊ መንገዶችን ለመመርመር ቁርጠኛ ነው።

የቡሪን ፖሊስ መምሪያ

የቡሪን ከተማ ከKing County የSheriff ጽ/ቤት ጋር ለፖሊስ አገልግሎት ውል ፈፅሟል። በBurien የተመደቡ የKing County Sheriff ሰራተኞች፣ የBurien Police Department ያቋቋማሉ፤ ወንጀልን በመከላከል እና የሚመለከታቸው የአካባቢ ህጎችን በማስፈጸም የማህበረሰቡን ደህንነት የማረጋገጥ ሃላፊነት አለባቸው። 

የBurien Police Department የኢሚግሬሽን ማስፈጸሚያ ጥረቶችን ለማመቻቸት መረጃን ማስተላለፍ ወይም የማህበረሰብ አባላትን ማሰርን ጨምሮ ከICE ማስፈጸሚያ ተግባራት ጋር አይተባበርም። 

የBurien Police Department፣ በBurien Municipal Code እና በKing County ደንብ (አጠቃላይ ትዕዛዞች መመሪያ 5.05.010፣ Burien Municipal Code 2.26.020፣ King County Code 2.15.020) የተፃፉትን ህጎች መከተል አለበት።

በKing County የSheriff የኢሚግሬሽን ፖሊሲዎችን የቪዲዮ መልእክት ይመልከቱ። 

በድንገተኛ አደጋ ግዜ

በአጣዳፊ ድንገተኛ አደጋ ውስጥ እንዳሉ ካመኑ፣ እባክዎ ወደ 911 ይደውሉ። 

በቡሪን ውስጥ የተመለከቱትን ልዩ ስጋቶች ለማካፈል ወይም እንቅስቃሴን ሪፖርት ማድረግ ከፈለጉ፣ ወደ King County የSheriff ጽ/ቤት የድንገተኛ አደጋ ያልሆነው መስመር በ (206) 296-3311 ማነጋገር ይችላሉ።

ምንጮች

ከታች ያሉት ማስፈንጠሪያዎች ለመረጃ አገልግሎት ብቻ የቀረቡ ሲሆን፣ ከCity of Burien የተሰጡ የህግ ምክር ተደርገው ሊቆጠሩ አይገባም። 

የአካባቢ ምንጮች

መብቶትን ይወቁ

የቤተሰብ ዝግጁነት ዕቅድ

የአሰሪ ምንጮች

በWashington State የሚገኙ የሕግ አገልግሎት አቅራቢዎች

ተጨማሪ መርጃዎች

የቡሪን ማህበረሰብ ማክበር

በ 202፣ የBurien City Council ውሳኔ ቁጥር 464 በማለፍ የአሜሪካን ብሄራዊ የእንኳን ደህና መጣችሁ ኔትወርክን በመቀላቀል የበለጠ እንግዳ ተቀባይ ለመሆን ቃል ገብቷል።

ከ 2021 ጀምሮ፣ የከተማው ምክር ቤት በመስከረም ወር አንድ ሳምንት በCity of Burien የእንኳን ደህና መጣችሁ ሳምንት እንደሆነ የሚያውጅ አዋጅ በማውጣት በBurien Town Square Park ውስጥ የእንኳን ደህና መጣችሁ ዝግጅትን ቡሪን አስተናግዳለች፤ በዚሁም በክልሉ ውስጥ ለአቀባበል ሳምንት ልዩ ዝግጅት ካደረጉ የመጀመሪያዎቹ ከተሞች አንዷ ነች።

ከ2022 ጀምሮ፣ የCity of Burien የማህበረሰብ ማገናኛዎች (Community Connectors) ፕሮግራም የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል እዲሁም ማስፋፋት ቀጥለዋል፤ ይህ ደሞ ከብዙ የባህል፣ የጎሳ እና የዘር ማንነቶች እና ተሞክሮዎች፣ ብዙ መጤ እና ስደተኛ ማህበረሰቦችን ጨምሮ፣ ማህበረሰባቸው እንዲበለጽግ የሚፈልገውን እንደ ጠበብት በሚያከብር ታማኝ ተሟጋች ሞዴል ላይ በመመስረት ነው።

በ 2023፣ የከተማው ምክር ቤት የLunar አዲስ ዓመትን ለማክበር እና የእስያ አሜሪካውያን ለቡሪን ማህበረሰብ ያበረከቱትን ብዙ አስተዋፅዖ ከፍ ለማድረግ አዋጅ አውጥቷል። 

በ 2025 ፣ የቡሪን የመጀመሪያ የማህበረሰብ የLunar አዲስ ዓመት ዝግጅት፣ በከፊል በ Burien's Neighborhood Grants Program የገንዘብ ድጋፍ የተደገፈ እና ከቬትናም ስደተኞች ጋር በመስራት በቡሪን ማህበረሰብ ማገናኛ የተደገፈ፣ በቡሪን ቤተ መፃህፍት እና በከተማው አዳራሽ መሰብሰቢያ ክፍል ተካሂዷል። 

Updated April 3, 2026